Breaking News
Home / Amharic / «ኤርትራ እምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋለሁ። አፍርሼ እቀላቅላታለሁ»

«ኤርትራ እምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋለሁ። አፍርሼ እቀላቅላታለሁ»

«ኤርትራ እምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋለሁ። አፍርሼ እቀላቅላታለሁ» አቢይ አህመድ አሊ ከአንድሺህ በላይ የብልጽግና ሰልጣኝ ካድሬዎች ስልጠና ላይ የተናገረው!!

እንቁዎቻችሁን እሪያ ፊት አትጣቱት፣ጭቃ ላይ ይረጋግጡታልና -መጽሓፍ ቅዱስ

*** ወንድወሰን ተክሉ***

📌 ከአንድሺህ በላይ የብልጽግና ካድሬ ሰልጣኞች «ምርቃት» ላይ ተላልፎ ያፈተለከ ምስጢራዊ ንግግር፦

ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቁንጮ አቢይ አህመድ ውስጥ ለውስጥ ሲያሽከረክር የቆየውን ጸረ ኤርትራ መንግስትና ጸረ የኤርትራ ሕዝብ ድብቅ ፖሊሲውን ሰሞኑን እያሰለጠናቸው ባሉት ካብኔት ምኒስትሮችና ከፍተኛ የብልጽግና አመራር ካድሬዎች ስልጠና ምርቃት ላይ በይፋ አውጥቶ አፈንድቶታል።

« የኤርትራን መንግስት እንደመሥሳለን። የኤርትራንም ሀገር አፍርሼ እቀላቅላታለሁ» በማለት አቢይ ድንግጥ ፍዝዝ ቅዝዝ ብለው ለሚያደምጡት ድንጉጥ ካድሬዎቹ በይፋ በመናገር በኤርትራ ላይ ያለውን ድብቅ ውስጣዊ ፖሊስን ይፋ ያደረገው እንዲህ በማለት ነው፦

«…. ኤርትራን ፣ ቀኑ መቼ እንደሆነ አልነግራችሁም እንጂ አፈራርሼ አምጥቼ እቀላቅላታለሁ።ኤርትራ የምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋታለሁ።አፍርሼ እቀላቅላታለሁ።» በማለት ከተናገረ በኋላ ለጥቆም

« ያኔ አሰብን ብቻ ሳይሆን የመላው ቀይ ባሕር ባለቤትም የምንሆን ስለሆነ ኤርትራ እምትባል ሀገር አትኖርም። እንድትኖርም አናደርግም» በማለት እንዴትና ለምን አንዱት ሉዓላዊ የሆነችን ጥሩ ወዳጅ ጎረቤት ሀገር ለማፍረስ እንደፈለገ ለሰበሰባቸው ምኒስትሮችና ታላላቅ የብልጽግና ካድሬዎች ተናግራል። ግን አንድም ትንፍሽ ብሎ ለምን እና እንዴት ብሎ የጠየቀው የለም። ድንፋታውን ግን በጭብጨባ አጅበውለታል።

የፋሺስታዊው ኦሮሙማው ቁንጮ አቢይ አህመድ በዚህ ብቻ አላበቃም። ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ ሲል ተናግራል።

« ለቀይ ባሕርና ለአሰብ ትልቅ እንቅፋት የሆነብን የኤርትራ ሕዝብ ሳይሆን ሕዝቡን ቀጥቅጦና አንበርክኮ እየገዛ ያለው መንግስት ነው» በማለት የአሰብን ወደብና ብሎም አጠቃላዩን የቀይ ባሕር ቀጠናን ብንወስድ የኤርትራ ሕዝብ ፍቃደኛና ደስተኛ ሆኖ ቄጤማ ጎዝጉዞ ፈንዲሻ እየበተና እልልልል እያለ እንደሚሰጠን አድርጎ በመግለጽ ሻእቢያ የሚባለው መንግስት ግን እንቢ አልሰጥም በማለት እንቅፋት ስለሆነብን ነው ስርዓቱን ደምሥሰን ኤርትራን ወደ ኢትዮጲያ የምንቀላቅለው ሲል የተደመጠው።

እንደ አቢይ አባባል ለአሰብ ወደብና ለቀይ ባሕር ብዬ ነው የኤርትራን መንግስት የማፈርሰውና ሉዓላዊ ሀገርነታን እንዲያከትም የማደርገው እያለ ሲለፋደድ ነው የተሰማው።

ንግግሩን ሲደመድምም «… ስራ እየሰራን ነው።እዚያ ያለውን አገዛዝ (አስመራ ያለውን ማለቱ ነው) ለማስወገድ የሚያስችለንን ስራ እየሰራን ነው። እዚያ ያለውን አገዛዝ እናስወግደዋለን » በማለት ከፊት ለፊቱ ለተኮለኮሉት ደናቁርት ድንዙዝና ሆዳም ካድሬዎች ምኒስትሮችና ዶክተርና ፕሮፌሰር ነን ተብዬዎች የቁም ምውታን ተናግራል።

የፋሺስታዊው ኦሮሙማ ስርዓት ቁንጮ ነኝ የሚለው አቢይ በኤርትራ ብቻ ሳያበቃ በደቡብ ከምትጎራበተን እጅግ የኢትዮጲያ ወዳጅ በሆነቺው ኬኒያ ላይም ፊቱን በማዞር «…የኬኒያን መንግስት በቀላሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አዘጋጅተን አጠናቀናል» በማለት የብራ መብረቅ የሆነ ዛቻን ተናግራል።

📌 የኬኒያን መንግስት ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት አካሂደን አጠናቀናል

« ኬኒያ .., የረባ የመቶ ዓመት ታሪክ የሌላት የበሬ ግንባር የምታክል ሀገር ስንዴና በቆሎ ስንልክላት ቆይተን የቀጠናው መሪ እኔ ነኝ ብላ እየተንጠራራች ነው። እኛ በላክንላት ችግኝ ተጠቅማ በአረንጋዴ ልማት የቀጠናው መሪ ነኝ ብላ የዓለም መሰብሰቢያ ለመሆን እየተንጠራራች ነው» በማለት በ2005 በአረንጋዴ ምርት በተለይም ከሰላሳ ሚሊዮን በላይ የጸደቁ ዛፎችን በመትከል የዓለም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆነቺውን ፕ/ር ዋንጋሪ ማታሂን ባፈራች ሀገር ላይ ችግኝ ልኬላት ሲል የተናገረው። ፋሺስቱ ስንዴና ባቄል ስንልክላት ቆይተን ብሎ ሲል በታሪኴ አንድም ግዜ ተርባ ስንዴን በእርዳታም ይሁን በግዢ ገዝታ ስለማታውቀው ኬኒያ ሳይሆን ስለማእከላዊ መንግስት የለሿ ሱማሊያ የሚናገር ነበር የሚመስለው።

በዚህም ሳያበቃ የዛቻ ንግግሩን በመቀጠል «… ኬኒያን እየመራ ያለው መንግስት በቀጠናው ከእኔ በላይ የለም ብሎ እየተንጠራራ ስለሆነ እሱን በቀላሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት እጠናቀን ጨርሰናል። የኬኒያን መንግስት በቀላሉ እንደመሥሰዋለን» በማለት ከኢትዮጲያ ጋር አንድም የድንበር ወግብ ከሌለባትና ከንጉሳዊው የዘውድ ስርዓት እስከ ዘመነ ኢሕአዴግ ባሉት ሶስት ተከታታይ መንግስታት የኢትዮጲያ ወዳጅ ኢትዮጲያን አክባሪና አፍቃሪ የሆነቺውን ጥሩ ወዳጅ ጎረቤታችንን ኬኒያን እንደመሥሳለን ብሎ ፊትለፊቱ ለተኮለኮሉት ከሺህ በላይ ታላላቅ የብልጽግና ካድሬዎች የለፈለፈው።

📌 የፋሺስታዊው ኦሮሙማ ስርዓት የክህደት ሰንሰለት ከሀገር ውስጥ አልፎ ድንበር ተሻግሮ በወዳጅ ጎረቤት ሀገራት ላይ መድረስ – የሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል የሆነበት ሁኔታ፦

የኢትዮጱያን ውስጣዊ ፖለቲካና ኢኮኖሚን ሁኔታ በቅርበት ለሚያውቅ – በተለይም መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ኋይል ባለቀበት የሰሜን ጦርነት ማግስት በአማራ ሕዝብ ላይ በተከፈተ ጦርነት በብርሃኑ ጁላ ወደ አማራ ክልል ከተላከው 100ሺህ በላይ ሰራዊት ውስጥ ከ80ሺህ በላይ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በተደመሰሰበትና ፋሺስቱ ጦርነቱን በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኋይል ተክቶ እየተዋጋ ያለበትን ቅርቃራ ሁኔታን የሚያውቅ ሰው ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ብሎ በማቃለል ሊያልፈው ይችላል። እንደዚህ ጸሓፊ እምነት ግን ይህ ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ሳይሆን ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው ጭንቀት በወለደው እብደቱ ውስጥ «እኔ እኮ አይደለም የአማራን ፋኖ ይቅርና ገና የኤርትራን እና የኬኒያን መንግስታቶችን ደምሥሼ አዲስ ግዛት የምመሰርት ፈርጣማ ገዢ ነኝ » ብሎ መናገሩን ነው የምረዳው።

የፋሺስቱ ድንፋታ ተራ ጭንቀት የወለደው የእብዳት ዛቻ ሳይሆን ተጨባጭ አመክኒዮ ያለው መሆኑን ለማየት የጠቀሳቸውን ምክንያቶች ማየት ይበቃል። በኤርትራ በኩል የጠቀሰው ምክንያት የአሰብና የቀይ ባሕር ጉዳይ ሲሆን ይህንን በተመለከተ በአማራ ላይ ጦርነት ከማወጁ መጋቢት ወር በፊት በየካቲት ላይ በፕሬዚዳንታ ሳህለወርቅ ዘውዴ በይፋ የተጀመረ የቀይ ባሕር ፖለቲካ የሚል ፕሮጄክት በይፋ መጀመሩን ለማስታወስ እወዳለሁ። ይህ የቀይ ባሕር መንግስታዊ ፕሮጄክት ይፋ ከመደረጉ በፊት ቢያንስ ከዓመት ከስድስት ወር በላይ ጥናት መንግስት ጥናት አድርጎበት ኢትዮጲያን የባሕር በር ባለቤት ለማድረግ አልሞ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ዓላማውን ለማሳካት ከኤርትራ መንግስት ጋር በድርድር አሊያም በኋይል ተጠቅሞ እንደሚያሳካ በይፋ መግለጹና እንዲያውም የኢትዮጲያን አየር መንገድ ባለቤትነት ድርሻ (ሼር አክሲዮን ባለቤት ) ለኤርትራ መንግስት እንደቀረበለት በመረዳት የዛሬው ድንፋታ ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ብቻ ሳይሆን አቅም ቢኖረው ሊፈጽመው ያቀደው ውጥኖቹ መሆናቸውን ነው መረዳት የሚቻለው።

በኬኒያ ጉዳይ ላይ ያነሳውንም አመክኒዮን ስንመለከት እውነትነት ያለበት ሆኖ ነው የምናየው። ኬኒያ ዛሬ በፋሺስቱ አቢይ ዘመን ብቻ ሳይሆን ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የምስራቃዊው የአፍሪካ ቀጠና በዲሞክራሲ፣ በኢኮኖሚ እድገት፣በአረንጋዴ ልማት፣በውስጣዊ የተረጋጋ ሰላም፣በጸረ አክራሪና አሸባሪ ኋይሎች ውጊያና በአፍሪካ የግዙፍ ስደተኞች መሸሸጊያ ሀገር በመሆን የቀጠናው መሪ የሆነች ሀገር ነች። ይህ አለሁ አለሁ ባይ ለሆነው እብዱ አቢይ አህመድ የሚዋጥ አልሆነምና በኬኒያ ላይ ያለው ቂምና ንዴት ኬኒያ እኔን እንደ ትልቅ ዝግባ ጋርዳኛለች በሚል የቅናት ንዴት የተመሰረተ በመሆኑ ዛቻና ፉከራው ተራ ጭንቀት የወለደው የእብደት ዛቻ ሳይሆን በትክክል ከመበለጥ የመነጨ ንዴት መሆኑን መረዳትና ማየት ያስፈልጋል።

በእርግጥ ኬኒያ ትልቅ ጥፋት አጥፍታለች። ያም ጥፋት ከዚህ ከፋሺስቱ የኦሮሙማ ስርዓት ጋር በመተባበር ፋሺስቱ ከዩክሬይን የተላከልንን የእርዳታን ስንዴ ዶላር ፍለጋ ለመሸጥ ሲቅበዘበዝ ኬኒያ ተስማምታ የመግዛታ ጉዳይ ትልቅ ጥፋትና ስህተት ፈጽማለች ብሎ ይህ ጸሓፊ ያምናል። የስንዴና ጥራጥሬ ምርት አቅርቦት እጥረት የሌላት ኬኒያ ለርሃብተኞች የተላከን ስንዴ ከፋሺስቱ እጅ ተቀብላ መግዛት አልነበረባትም ብዬ በግሌ አምናለሁ። የሆነው ሆኖ ግን ኬኒያ ፋሺስቱ እንዳላት የስንዴና የባቄላ እጥረት የሌላባት ሀገር ከመሆናም በላይ የዛፍ ችግኞችን በተመለከተ ግን ኬኒያ ለኢትዮጲያ ብትልክ እንጂ ከኢትዮጱያ የዛፍ ችግኝ የምትቀበል ሀገር አይደለችም።

በኬኒያ ችግኝ አፍልቶ ዛፍ መትከል በመንግስታዊ ዘመቻ የሚሰራ ስራ ሳይሆን በእያንዳንዱ ኬኒያ ደም ስር ውስጥ ያለ የዘልማድ ባሕላዊ ስራ ነው። በዚህም ምክንያት ነው የሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ በደን የተሸነችና በየመንገዱም ችግኝ እያፈሉ በሚሸጡ ሰዎች ተጥለቅልቌ የምትታየው። በተጨማሪም የሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ ከእንበሳ ጁምሮ ዝሆን ቀጭኔ ነብርና መሰል የዱር አራዊቶች የሚርመሰመሱበትን ናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክ (የናይሮቢ ደን) በዋና ከተማ ውስጥ በመያዝ የዓለማችን ብቸኛ ከተማ በመሆን የመንግስታቱ ድርጅት UN ጽህፈት ቤት ከኒዮርክና ከስዊዘርላንድ ጄኔቫ ቀጥሎ የናይሮቢው UNEP ጽህፈት ቤት ባለቤት ለመሆን የቻለቺው።

ስለዚህ እነዚህን እውነታዎችን ስንመለከት ከኢትዮጲያም አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እኔ ብቻ ነኝ ተደማጭ ሆኜ ፈላጭ ቆራጭ መሆን ያለብኝ ለሚለው ሁሉንም ኬኛ ባይ አቢይ አህመድ ኬኒያ በትክክል ዝግባ በመሆን እንደጋረደቺው በማየት ዛቻው ጭንቀት የወለደው ተራ የእብደት ዛቻ ሳይሆን መሰረታዊ የሆነ ምክንያት ያለውና ፋሺስቱ አቢይ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት መፈጸም የሚፈልገው ውጥን ምስጢሮቹ መሆኑን ነው የምረዳው።

ወደ ኤርትራ ልመልሳችሁና – የኢሱና የአቢቹ ስንብት በሚል ርእስ ስር የሁለቱን ሃይሎች ስንጥቃትን የጻፍኩት ባለፈው ዓመት መስከረም 2022 ላይ ሲሆን የተፈጠረው ልዩነት ግን አቢይ ሉዓላዊት የሆነችውን የኤርትራን ሀገር አፍርሶ እስከመጠቅለል የሚያደርስ ህልምና እቅድ ይፈጥራል ብዬ አለመገመቴን ልሸሽግ አይገባም።

በወዲ አፈወርቅ የሚመራው የኤርትራ መንግስት ለፋሺስታዊው የኦሮሙማው ብልጽግና ቡድን ትልቁን ውለታ የዋለ – ይህ ፋሺስታዊ ቡድን ቢያንስ ዛሬ ላይ ያደረሰውን ስልጣን ይዞ ይህን ያህል እንዲቆይ ያስቻለውን መደላድሎችን በመፍጠር የኤርትራን መንግስት የሚያክል ታላቅ ውለታ የዋለ የለም። ፋሺስቱ አቢይ ግን መጀመሪያ «ሀ» ብሎና ከማንም ቀድሞ በሰኔ ወር 2018 ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ፍቅሩን ድጋፉን በሰጠው የአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ክህደት በመፈጸም የጥቃት ዝናቡን ማዝነብ እንደጀመረ ሁሉ ለጥቆም ለአቢይ ወደ ስልጣን መምጣት ሌሎች ሳይገልጹ ታላቅ ድጋፉን በገለጸለት የትግራይ ሕዝብና ሰልሶ አማራ አቀፍ የድጋፍ ሰልፍ አድርጎ ፍቅር ክብርና ድጋፉን ለገለጸለት አማራ ሕዝብ ላይ የክህደት ሰንሰለቱን እያራዘመ መጀመሪያ በትግራይ ሕዝብ ላይ ለጥቆ በአማራ ሕዝብ ላይ እንደዘመተ ሁሉ አሁን ደግሞ የክህደት ሰንሰለቱን በማራዘም ባለውለታው በሆነው የኤርትራ መንግስትና የኤርትራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ድግስ መደገሱን – ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው በነበልባሉ ፋኖ ፋታ ነሺ ቅጥቀጣ የተጨነቀው አቢይ ጭንቀት በወለደው እብደቱ ይህንን በውስጡ ያመቀውን ምስጢር እንዲናገር መገደዱን ነው የምንረዳው።

በሀገረ ኤርትራም ሆነ በመላው ዓለም ያሉ ኤርትራዊያን እንደማንኛውም ሕዝብ በመንግስታቸው ላይ ጥያቄ ሊኖራቸው ይችላል። መንግስታቸውን በጽኑ የሚደግፉ እንዳሉ የሚቃወሙም ይኖሩ ይሆናል። ግን አይደለም በኤርትራ መንግስት አምነው መንግስትን የሚደግፉት ይቅርና መንግስት ላይ ጥያቄ የሚያነሱት እንኴን ሳይቀር በኤርትራ ሉዓላዊነት ላይ አንዳቸውም ጥያቄ የላቸውም። ሁሉም በሚያስብል ደረጃ የኤርትራ ሉዓላዊነት ተከብሮ ተጠብቆ መቀጠል አለበት ብለው የሚያምኑ ናቸው። ዛሬ ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቡድን ቁንጮ አቢይ ብድግ ብሎ ይህንን ሕዝብ ነው የኤርትራን መንግስት አፍርሼ በመቀላቀል ኤርትራ የምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋለሁ ብሎ ሲዝት መስማት የተቻለው።

እኛ አማራዊያን ግን ይህንን ፋሺስታዊን የእብደት ዛቻ – በወንድሞቻችን የኤርትራ ሕዝብና በኤርትራ መንግስት ላይ የተላለፈን ዛቻ በእኛ በአማራ ላይ የተላለፈ ዛቻና ጦርነት ብለን የምናየው በመሆኑ የኤርትራን ነጻነት ለመንጠቅ የሚደረግን ማንኛውንም ዓይነት ዘመቻና ፕሮፖጋንዳን በጥብቅ የምናወግዝና አጋርነታችንንም ለኤርትራዊያን በማድረግ ወራሪውን እንወጋለን እንጂ አንድም የአማራ ልጅ በጸረ ኤርትራ ዘመቻ ላይ የማይሳተፍ መሆኑን አስረግጠን በአቌም ደረጃ እንደ ሕዝብ የምንገልጸው አቌማችን ነው።

📌 እንቁዎቻችሁን እሪያ ፊት አትጣሉ። ጭቃ ላይ ይረጋግጡታልና። የእግዚ አብሔር ቃል

የአቢይ ክህደት ሰንሰለት ማለቂያ የለውም። የአቢይ ተክለ ስብእና የተገነባው በክህደት፣በውሸት፣በጥላቻ ቅናት የተገነባ እሱ ራሱ ህይወት ያለው ክህደት ቅናት ጥላች ውሸት ሆኖ ስጋ ለብሶ የተከሰተ በመሆኑ ያከበሩትን የደገፉትን ከጎኑ ቆመው የረዱትንና ያገዙትን በሙሉ ከግለሰብ እስከ ማሕበረሰብ ከድርጅት እስከ የሀገር መንግስታት ያሉትን በሙሉ በሚቻለው መጠንና አቅም ሁሉ አንድ በአንድ ተመልሶ የሚበላ ሰው ነው።

ጠቢበኛው ሰለሞን እንቁዎቻችሁን እሪያ ፊት አትጣሉ ጭቃ ላይ ይረጋግጡታል ብሎ ሲናገር እንቁ ማለት – እውነት፣እምነት፣ፍቅር፣ክብር፣ታማኝነና ውለታ ሲሆን እሪያ ማለት ደግሞ እንሥሳው ሳይሆን እውነትን፣ፍቅርን፣እምነትን፣ክብርን፣ታማኝነትን እና ውለታን የማያውቅና የማያከብር ውለታ ቢስ የሆነ ሰው ነኝ ባይ ግን ስብእናዊው ግብሩ እንሥሳዊ የሆነ እንደ አቢይ አህመድ አይነቱን ነው እሪያ ብሎ የገለጸው።

እኛ አማራዊያን ግን በእጅጉ ተለይተን ከምንታወቅባቸው እንቁ እሴታዊ ስብእናዎቻችን ውስጥ ውለታን አክባሪነት፣ ለእውነትና ለእምነት ጹኑ አክባሪነትና ተገዢነት የምንታወቅበት የግብር መገለጫዎቻችን ሲሆን ይህን ድንቅ እንቁ ስብእናን ለማይገባው ሰው መሳይ ግን ግብሩ እሪያ ለሆነ ፈጽሞ መግለጽና መስጠት እንደሌለብን የፋሺስቱን ኡቢይ እኩይ ምግባር በጥሩ አስተማሪነት ተምሳሌት በመጥቀስ እደመድማለሁ።አብእቃሁ።

*******++++++++*******++++++*****

💎 💎 💎
ለበለጠ መረጃና ብሎም ለተሳትፎ የጋሻ ሚዲያን ዓለም አቀፍ የመወያያ ቴሌግራም ቻናልን በመቀላቀል መረጃዎችን በማቀብልና በመቀበል ሂደት ላይ የበኩላችሁን ድርሻ በማበርከት ይሳተፉ 👇👇👇

https://t.me/GMMediad

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.