Breaking News
Home / Amharic / አብይ አህመድ ጦሩን ከትግራይ አስወጥቶ ለምን ወደ አማራ ክልል አስገባው ?

አብይ አህመድ ጦሩን ከትግራይ አስወጥቶ ለምን ወደ አማራ ክልል አስገባው ?

# የአብይ መግስት ተኩስ አቆሚያለሁ ካለ ጀምሮ ሕወሃቶች ግን ተኩስ አናቆምም ብለው ዉጊያ እያደረጉ ነው፡ በአሻጥር ፣ የአማራ ልዩ ኃይል በኋላ የመከላከያ ሰራዊት እንዲለቅ ታዞ ኮረምን ብሎም አላማጣን ፣ በአጠቃላይ እንዳለ ራያን ተቆጣጥረዋል።
# ዉጊያውን ከራያ አልፎ ወደ አፋር ክልል ዞን አራት፣ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋን እና ዋግመራ ዞን ወስደዉታል። በምስራቁ ግንባር ላለፉት 3 ቀናት ዉጊያ ሲደረግ የነበረው በነዚህ ቦታዎች ነበር።
# በአሁኑ ወቅት በዋግመራ ዞን የአበርገሌን ወረዳ በሕወሃት ስር ነው ያለው።፡ቁጥሩ ቀላል የማይባል ኅዝብ ከቅይው ተፈናቅሎወደ ሰቆጣ እያመራ ነው። የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ ተብሎ የተደረገ ውሳኔ የዋግመራ ገበሬ እንዳያርስ አድርጎታል። በዋግመራ ያለው ሁኔታ መግስት ከሕዝብ ደብቋል።
# በአፋርና በሰሜን ሸዋ ቆቦ አካባቢ ወያኔ ከወያኔዎች ጋር ከፍተኛ ዉጊያ ተደርጓል።፡በነዚህ አካባቢ የመቆየት እድላቸው በጣም የመነመነ ነው። ብዙ የሕወሃት ታጣቂዎች በሰሜን ወሎም በአፋርም እያለቁ መሆኑ ዕተገለጸ ነው።
# በጠለምት ዉጊያ አለ። ወያኔዎች ገፍተው እንዳይሄዱ በዚያ ያለው የአማራ ሕዝብዊ ሰራዊት ገትሮ ይዟቸዋል። ብዙ ሞክረው የተወሰኑ የጠለምት አካባቢዎች እንዳያዙ ነው ግን በቅርቡ ከተእዜ ማዶ ይገፋሉ የሚል ግመት ነው ያለው።
# ወልቃይት እጅግ በጣም ብዙ ጊዜ ወያኔዎች ዉጊያ ከፍተዋል። በሱዳን በኩል ኮሪዶር እንዲኖራቸው ሁመራ ለመያዝ አስበው። ሆኖም ሁሉም ጥረታቸው ሊሳካ አለመቻል ብቻል ሳይሆን በ እያንድንዱ ጊዜ ከፍተኛ ጉዳትን እልቂት ነው የደረሰባቸው።
በራያ ግንባር፣ በጠለምት፣ በወቅላይት በዋናነት እየተንቀሳቀሰ ያለው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ነው። መከላከያ ዉጊያ ላይ አልተሰማራም። ስላልታዘዘ። ሆኖም ግን በተለይም በራያ ግንባር በቆቦ አካባቢ በተደረገው ዉጊያ መከላከያ ለአማራ ሕዝባዊ ኃይል የተወሰነ የአየር ድጋፍ አድርጓል።
በአፋር ግንባር የአፋር ልዩ ኃይሎች በዋናነት ዉጊያውን ይመሩት የነበረ ሲሆን፣ የኦሮሞ ልዩ ኃይል አባላትን እገዛ አድርገዋል። መከላከያም ወያኔዎች የጅቡቲን መስመር ሊዘጉ ይችላሉ ከሚል ፍርሃይ መሰለኝ አየል ባለ መልኩ በአፋሩ ጦርነት ተሳትፏል።
በአሁኑ ወቅት ወያኔዎች በአፋር ሙሉ ለሙሉ የተደመሰሱ ይመስላል። በሰሜን ወሎ የተገኘው አንጸባራቂ ድል፣ የአማራ ሕዝባዊ ሰራዊትም ብቃት ያላቸውና የሚታመኑ የጦር አመራሮችና ስትራቲጂስቶች እንዲመሩት ምደረጉ ሲጨመርበት ፣ በቅርቡ ሰራዊቱ ትልቅ መነሳሳትና ሞሜንተም እንደሚያገኝ የሚታወቅ ነው። ወያኔውች ከጠለምትና ራያ ሙሉ ለሙሉ እንዲወጡ የመደረጉ እድል በጣም የሰፋ ነው።
ትልቁ ጥያቄ ከዚያ በኋላስ የሚለው ነው ።

-Girma Kassa

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.