Breaking News
Home / News / በግፍ የታሰረው ኢንቬስተር ተፈታ።

በግፍ የታሰረው ኢንቬስተር ተፈታ።

ዛሬ ለዚህ ፅሁፍ ርዕስ መስጠት ከበደኝ፣ ስፅፈው አንጀቴ እያረረ ነው። በፈጠራችሁ ንፁህ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ Share አድርጉት ቢያንስ 2 ሚሊየን ግዮናዊያን ይዩት ይማሩበት።
~~~~~~
ዛሬ ነፃ የተባለውና ለ8 ወራት በግፍ ታስሮ የነበረው ኢንጅነር ዳንኤል ግዛው ካምፖኒ ድርጅት በአመት 100ሚሊየን ዶላር ወይም ወደ 4ቢሊየን የሚጠጋ ብር አመታዊ ገቢ ነበረው(አሁን ያለበትን ቁመና አናቅም)
~~~~
በመጀመሪያ የዛሬ አመት አካባቢ በብአዴን ግራ ክንፍ አክቲቪስቶቹ እነ @Miky Amhara እና መሰሎቹ አማክኝነት የስም ማጥፋት ተካሄደበት፣ በደምብ ወንጀለኛ ሌባ ተባለ ሴራው ያልገባው መንጋም ተከተለ፣ ይሰቀል አለ። ሴራው ግን ግዮናዊያንን ከኢኮኖሚ የማስወጣት እንቅስቃሴ ነበር።

በነ በረከት ስምዖን መዝገብ የሙስና ወንጀልም ታሰረ፣ እንግዲህ አስቡት አንደ አለም አቀፍ ምሁርና ኢንቨስተር ያለወንጀሉ ለ27 አመት ደም ከጠቡት ጋር ሲታሰር።

ለመሆኑ በአለም አቀፍ መድረክ አንቱ የተባለው ኢንጂነር ዳንኤል ግዛው ማን ነው?

በጎጃም ቢቡኝ ወረዳ የተወለደው እንጅነር ዳንኤል ግዛው ትምህርቱን የተማረው አሜሪካ እና ፖላንድ ሲሆን በጀነራል ሞተርስ ፣ በጀነራል ኤሌክትሮኒክስ ፣ በፎርድ ሞተርስ እና ኤሌክትሮኒክስ ትምህርት ቀስሟል።

ኢንጂነር ዳንኤል ግዛው ባለሀበትና ሊቅ ነው። የተሻለ ትምህርት ፍለጋ አሜሪካንን ሲረግጥ ገና የ17 ዐመት ልጅ ነበር። ፋታ የማይሰጠውን የምዕራቡን ዐለም ህይወት ተጋፍጦ ‹ኢንጂነር› ተብሎ ያሰበውን አሳክቷል፡፡ ፖላንድ ከሚገኘው Gdansk ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ በኤሌትሪካል አንጂነሪንግ ተምርቋል፡፡ በሚኖርበት አሜሪካ ደግሞ ‹በኤሌትሪካል ሞተር› ስፐሻላይዝድ አድርጓል፡፡ ወደ ምርምሩ አጋድሎ በአገኘው ውጤት፣ ከአርባ በላይ የፈጠራ ‹ፓተንቶች› በዩንይትድ ስቴትስ በስሙ አስመዝግቧል። በአሜሪካ የጄነራል ሞተርስ ካምፓኒና በሌሎች የምህንድስና ዘርፎችም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የበቃ፣ ስመ-ገናና የተከበረ ሰው ሆኗል። (ፒ.ኤች.ዲውንም እየሰራ ነበር)
ኢንጂነር ዳንኤል ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ ጥቂት ዐመታት አልፈውታል፡፡ ዘውትር “በሀገሬ ውስጥ ለውጥ አመጣለሁ!” የሚል እምነት እንደነበረው ወዳጆቹ ያስታውሳሉ።
።።። ፡፡
ዳንኤል አገር ቤት ከገባ በኋላ ‹ዲቬንተስ› የተሰኘና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ኢንጂነሮችን(ከ131 በላይ) ያካተተ ድርጅት አቋቁሞ ነበር። ድርጅቱ የተለያዩ የምህንድስና ውጤቶችን አምርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል። በተጨማሪም ጣጣቸው አልቆ ለምርት ከተዘጋጁ የፈጠራ ሥራዎቹ መሀል የ‹ስማርት ውሃመቆጣጠሪያ እና የመብራት ቆጣሪ› ይጠቀሳሉ። የ‹ስማርት መብራት ቆጣሪው› ገና ከጅምሩ ከኢትዮጵያም አልፎ የደቡብ አፍሪካና የሳዑዲ ዐረብያን ቀልብ በመሳቡ፣ ሁለቱ አገራት ከ#ግማሽ_ቢሊዮን_ዶላር በላይ ለሚያወጣ ግዢ ኮንትራት ፈርመው፣ ምርቱን ለማጓጓዝ በተስፋ እየጠበቁ ነበር፣ የድርጅቱ ወርሃዊ ገቢው 4ቢሊየን ብር ነበር። ምን ዋጋ አለው?! ኢንጂነር ዳንኤል ግዛው ባልዋለበት በሴራ ተለቅሞ ለግፍ እስር ተዳረገ እንጂ።

ለግዞቱ የተሰጠው ምክንያት በእነ አቶ በረከትና ታደሰ ጥንቅሹ የሚመራው “ጥረት” የተባለው የዐማራ ድርጅት አቀነባባሪነት፣ ሳይንቲስቱ በቅጡ-ባልተረዳው በማያቀው የሙስና መረብ ገብተሃል በሚል ነው። ባለፈው ዐመት አጋማሽ የክልሉ መንግሥት እነ በረከትን እስር ቤት ለመክተት በተንቀሳቀሰበት ወቅት፣ ዳንኤልንም ‹ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ…› አድርጎታል፡፡

ከሩብ ክፍል ዘመን ፈቀቅ ላለ ጊዜ የሥርዐቱ ቁንጮ የነበሩት የአቶ በረከትና ግብረ-አበሮቻቸው መታሰር አስገራሚ የሚሆንበት ነገር እንደሌለው ይገባኛል፡፡ ይሁንና በሰው አገር ተምሮ ‹አንቱ› ተብሎ በቅንጦት መኖር የሚችልበትን ዕድል ገፍቶ፣ አገሩን ለማገልገል የመጣ ቅን-አሳቤ በማያውቀው የቢሮክራሲ ትብታብ ተጠልፎ ለእስር ሲዳረግ ማየት ማሳዘኑና ልብ-መስበሩ አይቀርም። በነገራችን ላይ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ለሙከራ እየተጠቀመበት ያለው ‹ስማርት ቆጣሪ› የዚህ ግፉአን የፈጠራ ሥራ እንደሆነ ልብ ይሏል። እስከአሁን በተገኘው ውጤትም ይህ ቆጣሪ ምርጥ መሆኑ ተመስክሮለታል። ድርጅቱም ከ‹ዱቬንተስ ካምፓኒ› ጋር ተጨማሪ ስምምነት ለመፈራረም በዝግጅት ላይ እያለ፣ በሚያዚያወር 2011 ዓ.ም ኢንጂነር ዳንኤል ከአዲስ አበባ በዐማራ ክልል ልዩ ኃይል ቁጥጥር ሥር ውሎ (ቀለል ሳደርገው ነው እንጂ፣ ነገሩን የሚገልጸው ‹አፈና› የሚለው ቃል ነው) ወደ ባሕር ዳር ተወስዷል። ኢንጂነር ዳንኤል ግዛው ለምን ታሰረ? የሚለውን ጥያቄ ትንሽ ላፍታታው፡፡
‹ጥረት› የተባለው የዐማራ ክልል የንግድ ድርጅት የተቋቋመበት ዓላማን በተመለከተ በመመስረቻ ደንቡ ላይ የሰፈረው የሕዝቡን ችግር ስለመቅረፍ ቢሆንም፤ በተግባር ግን ባለሥልጣናቱ ተምነሽንሸውበታል ማለቱ ለእውነታው የቀረበ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በግንባር-ቀደም ተጠያቂነት ከአቶ በረከትና አቶ ታደሰ በተጨማሪ የተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በሙስና እና የሕዝብን ሀብት በማባከን ወንጀል ተጠርጥረው እስር ቤት ገብተዋል። የኢንጂነሩ ጉዳይ ግን ለየት ይላል። ወቅቱ ‹ስማርት ቆጣሪ›ውን በዐለም ገበያ ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም ለ‹ጥናትና ምርምር› ከባንክ የተበደረውን ገንዘብ ለመክፈል የሚሯሯጥበት ጊዜ ነበር። የፈጠራ ሥራው ‹ስማርት ቆጣሪ›ም በሙከራው አስገራሚ ውጤት በማስስመዝገቡ ደስታው ጨምሯል። ይሁንና የግዢ ኮንትራት ለፈረመው የኢትዮጵያ መብራት ኃይል በብዛት ለማምረት የሚያስችለውን ጥሬ እቃ ለመግዛት ተጨማሪ ገንዘብ እያፈላለገ ነው። በዚህ መሀል ከውጪ ያስመጣቸውን እቃዎች በፍጥነት ለማጓጓዝ፣ ከመንግሥት ጋር ቀጥታ ግንኙነት የነበረው “ጥረት” ከኢንጂነሩ ጋር አብሮ ለመስራት ይስማማል። የሚጠበቅበትን ገንዘብ በመክፈልም ‹ሼር ሆልደር› ሆኖ ይቀላቀላል። ይሁንና ዘግይቶ የደረሰው ጥረት፣ ቀስ በቀስ በካምፓኒው ላይ እንደ ዘንዶ መጠቅለል ቋመጠ፣ ኢንጂነሩ ‹ጥረት› በካምፓኒው የውስጥ ሥራ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም፣ አለዚያም ገንዘባቸውን መልሶ የኢንቨስትመንት ውላቸውን እንደሚሰርዝ በቃልም በደብዳቤም ያስጠነቅቃል፡፡ ወዳጄ የዋሃ ነበር፡፡ አሜሪካን አገር የሚያውቀው የሕግ-የበላይነት አዲስ አበባም የሚሰራ መስሎታል፡፡ ሕግን ተከትሎ ከሰጠው ማስጠንቀቂያ ያተረፈው ነገር ቢኖር በጉልበተኛ ሹማምንት ጥርስ መነከስ ብቻ ሆነ።

ዳንኤል በኢትዮጵያ ሥር-የሰደደው የመጠላለፍ ጨዋታ፣ ሴራ-ተኮር ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካ ገና አልገባውምና፣ በመንግሥት-ማሊያ የሚጨዋተው ‹ጥረት›፣ የትርፍ ተካፋይ ለመሆን ሲጠይቀው፣ ‹‹ለግዜው ሥራውን ለማጣደፍ ያስችለናል›› በሚል መንፈስ ገርበብ ያደረገለትን በር፣ በርግዶ በመግባት የ‹ዲቬንትስ› ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ አረፈው። ጥረት በውሉ መሰረት የሚያስተዳድራቸው 22 የንግድ ድርጅቶቹ ተደምረው ከሚያገኙው ሁሉ የበለጠ ከዚህኛው ሼሩ እንደሚያፍስ ያውቃል። በዚያ ላይ ‹ዲቨንተስ ካምፓኒ› ወደፊት ከሚሸጣቸው ‹ስማርት ቆጣሪ›ዎች የሚገኘው ትርፍ የሚያጓጓ ነው። ቆጣሪው በብዛት ሲመረት፣ በተለይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል በሚሊዮኖች የሚቆጠር መግዛቱ ከወዲሁ የተረጋገጠ ነው። ደቡብ አፍሪቃ እና ዐረብ አገራት ቆጣሪውን ለመሸመት ያደረባቸው ጉጉት ሲጨመርበት ብዙ ቢሊዮን ገንዘብ መታፈሱ አይቀርም። የአገሪቱን የዶላር ራሃብ ማስታገሱም ተገማች ነው። ነገሩ ‹አልጠግብ ባይ…› ሆነና፣ ጥረቶች በለመዱት መንገድ ኢንጂነር ዳንኤልን ከጨዋታ ውጪ አድርገው፣ ካምፓኒውን ለመጠቅለል ሴራ ይጠነስሱ ጀመር፡፡
እጃቸውን ያሟሹትም ካምፓኒውን ኦዲት በማስደረግ ሰበብ ጉድለት እንዲገኝበት አድርጎ የኢንጂነሩን ምርጫ በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ መቀርቀር ላይ ያውጠነጥናል፡፡ አንድም በወህኒ መማቀቅ፣ አሊያም አገር ጥሎ መጥፋት፡፡ ከዚያም ግዙፉን ፕሮጀክት በተናጠል ተቆጣጥሮ ሚሊዮን ዶላሮችን መቁጠር። ነገር ግን የኦዲት ሪፖርቱ እንከን-የለሽ ሆኖ በመገኘቱ ሴራው ከሸፈ። ግዴለም! ‹ነገም ሌላ ቀን ነው› በሚል አደፈጡ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ካምፓኒው ከመብራት ኃይል ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት ራሱን ከእዳ ነጻ ለማድረግ፣ በኢንቨትመንት ከተገኝው ገንዘብ ላይ ለአቢሲንያ ባንክ የነበረበትን የበርካታ ሚሉየን ሚሊዮን ብር ብድር ክፍያ ፈጸመ። ይህ ሁነት መሃንዲሶቹንና ሠራተኞችን ሲያስደስት፤ “እዳውን መክፈል ሲያቅተው ድርጅቱን እንወርሳለን” በሚል ቀቢፀ-ተስፋ ሲጠብቁ የነበሩትን የጥረት ኃላፊዎች በብርቱ አስቆጣቸው።
በሌላው የድራማ ማዕዘን ደግሞ ኢንጂነር ዳንኤል ከጥቂት ቀናት በኋላ ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል ጋር ተጨማሪ የሽያጭ ውል ለመፈራረም ቅድመ-ሁኔታዎች እያለቁ ነው።
ይህ ቆጣሪ ሙሉ ለሙሉ በሥራ ላይ ሲውል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በሁሉም ክልል የሚገኙ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይታወቃል። ኢንጂነሩና ባልደረቦቹ በዚህ አይነቱ መንፈስን በሚያረካ የደስታ ስሜት ከመሞላታቸው በዘለለ፤ ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል ጋር ስምምነቱ ሊፈረም ከጫፍ ደርሷል፡፡ እንደው መርዶ መናገር ምንኛ ከባድ ነው?! ብቻ በዚህ ወቅት ነው የዐማራ ክልል ልዩ ኃይል አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ ኢንጂነር ዳንኤል ግዛውን በካቴና አስሮ ወደ ባህር ዳር ፊቱን የመለሰው። አሰረው የጥረት የመንደር ቡድን ንፁሁና ምሁሩን ግዮናዊ ወደ ግዞት ወረወረው።

ዛሬ ዳንኤል በፍርድ ቤት ነፃ ነህ ተብሏል፣ ምንም ወንጀል አይገኝበትም። በአደጉት ሀገራት ቢሆን በቢሊየን የሚቆጠር ካሳ ይከፈለው ነበር ግድ የለም ገንዘቡን ነገ ያገኘዋል፣ የግዮን ልጆች ግን ተማሩበት።

መውጫ-
እንደ ኢንጅነር ዳንኤል ሁሉ በህወሓት እና በዱቄት ተሸካሚያቸው ሰዎች ከገበያ የወጡ፣ የተሳቀቁ የጎጃም ምሁራን፣ ባለሃብቶች ተቆጥረው አያልቁም። ከዚህ ሁሉ ግፍ አምልጠው ዛሬ ጥቂት ሀብት ያፈሩትን ደግሞ እየዘለፏቸው ነው።

ማስታወሻ-
በጥረት ኮርፖሬሽን ስር ያሉ 22+ ካምፖኒዎች በጠቅላላ የሚመሩት በደቡብ በጌምደር ጎጠኞች ብቻ ነው፣ ሁሉም የቦርድ አባላትም የደቡብ በጌምድር ሰዎች ናቸው ። ለአክቲቪስቶቻቸው ቀለብ የሚሰፈርም ከዚህ ተቋም ነው።

share ማድረግ እንዳትረሱ!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.