በደህንነት አካላት ታፍነው ደብዛቸው ጠፍቶ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ከ28 ቀናት ቦኋላ ገላን በሚገኝ የልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተገኙ!
ከታፈኑት መካከል የምኒልክ ሆስፒታል፣ የአለርት ሆስፒታል፣ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ከፍተኛ ሀኪሞች ይገኙበታል።
መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክራችኋል በሚል ለ28 ቀናት በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በሚገኘው የልዩ ሀይሉ ካምፕ ውስጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፀምባቸው መቆየቱን ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።
ከታሣሪዎቹ መካከል የእግር እና የእጃቸው ጥፍር በፒንሳ የተነቀለ፣ጀርባቸውን በኤሌክትሪክ የተገረፉ በዱላ እና በክላሽ ሰደፍ የተደበደቡ መኖራቸውም ተገልጿል።
ከ28ቱ ሰዎች ውስጥ አንዷ ሴት ስትሆን በተደጋጋሚ በቡድን ሲደበድቧት መሰንበታቸውንም እስረኞቹ ተናግረዋል።
በተፈፀመባት ድብደባ በአፍና እና በአፍንጫዋ ደም ሲፈሣት መቆየቱንና እስከአሁንም ህክምና ማገኘት እንዳልቻለች የአማራ ድምፅ ለማረጋገጥ ችሏል።
እስረኞቹ ለ28 ቀናት በጨለማ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን እና በቀን አንድ ግዜ ብቻ ደረቅ ዳቦ ሲቀርብላቸው እንደነበርም ተናግረዋል።
28ቱም ከአድስ አበባ ከተማ የተወሰዱ ሲሆን በምርመራ ላይ ሲጠየቁ የነበሩት የአማራን ህዝብ አደራጅታችሁ መንግስትን ለመገልበጥ እየሰራችሁ ነው፣ ይህ ደግሞ አይሳካላችሁም፣ ከፈለጋችሁ አዲስ አበባን ለቃችሁ ውጡ የሚል እንደነበር ነው የገለፁት።
በህቡዕ ተደራጅታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሳችሁ ነው፣ አማራ ክልል ድረስ አደረጃጀት ዘርግታችሁ ሁከት እና ብጥብጥ ቀስቅሳችኋል፣ ማነው መሪያቹህ? በሚል በጦር መሣሪያ እና ስለታማ መሣሪያ በተለይ አንገታቸው ላይ በማድረግ ሲያስፈራሯቸው እና ምርመራ ሲካሄዱባቸው መሰንበቱን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ እናንተ ኦሮሞ ጠል ናችሁ፣ ይህ ስርአት ወደዳችሁም ጠላችሁም የኦሮሞ ስርአት ነው፣ በአዲስ አበባ መኖር ከፈለጋችሁ ለጥቀጥ ብላችሁ የኦሮሞን ህዝብ እግር ማጠብ አለባችሁ፣ ካልፈለጋችሁ ግን ከተማዋን ለቃችሁ ውጡ በሚልና ሌሎች ፅያፍ ስድቦችን መርማሪ ፖሊሶች ሲሰድቧቸው እንደነበር ነው የተናገሩት።
ከታሳሪዎቹ መካከል 28ቱ ከ28ቀን ቦኋላ ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አሁንም እዛው ገላን በሚገኘው የልዩ ሀይሉ ካምፕ ድብደባ እየተፈፀመባቸው ያሉ የአማራ ተወላጆች መኖራቸው ተጠቁሟል።
ከእስረኞቹ መካከል በተለይ አንደኛው በምርመራ ላይ በተፈፀመበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በተኛበት እንደሚፀዳዳ እና ራሱን መቆጣጠር እንደተሳነው እንዲሁም ለአዕምሮ ህመም መዳረጉን ነው የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የአማራ ድምፅ ሚድያ ማረጋገጥ የቻለው።
28ቱ እስረኞች ግንቦት 18/2015 ዓ/ም ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ይቀርባል፦
1ኛ፦ቢኒያም አለማየሁ(ሲቪል ኢንጂነር)
2ኛ፦መላክ ምሳሌ (መሐንዲስ)
3ኛ፦ዳዊት ይፍሩ(ዋና ኢንስፔክተር)
4ኛ፦ጌጤ አመኑ(ሳጅን)
5ኛ፦ጌታወይ ታደሰ(ኮማንደር)
6ኛ፦አወቀ ስንሻው(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ)
7ኛ፦ ይመር ምንተስኖት(ሲቪል ኢንጂነር)
8ኛ፦ጌታነህ ብርሀኔ(ጤና መኮነን/ምኒልክ ሆስፒታል)
9ኛ፦አብርሃም መልካሙ(ሳይካትሪስት/የአለርት ሆስፒታል)
10ኛ፦ምኒበል ጀግኔ(ሳይካትሪስት/የጦር ሃይሎች ሆስፒታል)
11ኛ፦ኤርሚያስ መኩሪያ(phd)
12ኛ፦ደበበ ባሻህውረድ(ባለሃብት)
13ኛ፦ንብረት አበጀ(የግሮሰሪ ባለቤት)
14ኛ፦ይልማ በዛብህ(በቦሌ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ)
15ኛ፦ቅድስት ከበደ(የቤት እመቤት)
16ኛ፦ፍቃዱ መንግስቴ(ፋርማሲስት/ዘውዲቱ ሆስፒታል)
17ኛ፦አንዷለም አሻግሬ(እንስፔክተር)
18ኛ፦ማናየ አየለ(MBA/የግል ስራ)
19ኛ፦አለም ሁሉምጤና(መምህር)
20ኛ፦ይስሃቅ አይቼው(መርጌታ)
21ኛ፦ጌታነህ ታከለ(የአየር መንገድ ሰራተኛ)
22ኛ፦እንዳልካቸው እሸቱ(የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ሰራተኛ)
23ኛ፦ክበር አለማየሁ(መሐንዲስ)
24ኛ፦ባሳዝን እርገጤ(የአንበሣ ባስ አሽከርካሪ)
25ኛ፦መብራቱ አበራ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)
26ኛ፦ውበት አካል(ጥበቃ)
27ኛ፦ዜና ሀይሉ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)
28ኛ፦ሰለሞን ደሴ(ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አካውንታንት)
እነዚህ የአማራ ተወላጅ የሆኑ 28 ሰዎች ለ28 ቀናት ገላን በሚገኘው የልዩ ሃይሉ ካምፕ ውስጥ በጨለማ ክፍል ታስረው የግፍ አይነት ሲፈፀምባቸው የነበሩና ከግንቦት 18/2015 ዓ/ም ጀምሮ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ ናቸው።
👉 እነዚህ የአማራ ተወላጆች በ28 ቀናት ውስጥ የተፈፀመባቸው የግፍ አይነት፦
1ኛ የተፈፀመባቸው አካላዊ በደል፦
፦ግርፋት
፦በኤሌክትሪክ (shok)
፦ስብዕና የሚነኩ ስድቦችን እየተሰደቡ ግድግዳ መግፋት
፦በክላሽ ሰደፍ ድብደባ
፦ጥፍራቸውን በፒንሳ መነቀል
፦ምግብ መከልከል
፦አድራሻቸው መሰወር(ቤተሰብ ያሉበትን እንዳያውቅ)
2ኛ የተፈፀመባቸው ስነልቦናዊ በደል፦
፦የምኒልክ ቆማጣዎች
፦የታሪክ ሌቦች
፦መጤዎች
፦ተስፋፊዎች
፦ቁምጣ ለባሾች
፦የምትጠይቁትን የማታውቁ
፦ወራሪዎች
፦ለእናንተ ስልጣን ከምናጋራ ኢትዮጵያ ትፍረስ
፦አዲስ አበባ የኛ ናት ስሟም ፊንፊኔ ነው
፦ወያኔ ቤታችሁ ድረስ መጥቶ ሚስትህን፣ልጅህን፣እህትህን እና እናትህን ሲደፍር የት ነበራችሁ?…እኛነን ያዳናችሁ
፦እንዴት ከኦሮሞ ጋር ትፎካከራላችሁ?እናንተ የኦሮሞን ያክል መብት ሊሰጣችሁ አይገባም
፦ገና ጨፍጭፈን ከምድረገፅ እናጠፋችኋለን የሚሉ ስድቦች እና ማስፈራራቶች ናቸው።
👉በአሁን ሰአት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደውን አፈና በበላይነት የሚመሩ እና የሚያስተባብሩ ተቋማት፦
፦የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ
፦የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ
፦ቴሌ ኮሙዩኒኬሽን
፦የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
፦የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
፦የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
፦የገላን ፖሊስ መምሪያ
፦በኦሮሞ ህዝብ ስም የተቋቋሙ የቢዝነስ ተቋማት እና የኦሮሞ ባለ ሀብቶች
፦እራሱን “የኦሮሚያ ሲኖዶስ” በሚል የሚጠራው ተቋም
👉የአማራ ተወላጆችን በማሳፈን፣ ምርመራውን በመምራት እና አሰቃቂ ድብደባ እንዲሁም ግፍ እንዲፈፀምባቸው ትዕዛዝ በመስጠት የሚሳተፉ፦
፦ደመላሽ ገ/ሚካኤል(የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር)
፦ተመስገን ጥሩነህ(ከብሔራዊ ደህንነት)
፦መላኩ ፈንታ(ከወንጀል መከላከል ቢሮ)
፦ዘላለም መንግስቴ(የወንጀል ምርመራ ኃላፊ)
፦አበራ ወንዴ(የኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ)
፦አህመድ አብደል(የኦፕሬሽን መምሪያ ም/ኃላፊ)
፦ኮ/ር ኢብራሂም(የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ)
፦ኮ/ር ኢቻራ(የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ም/ኃላፊ)
፦ምክትል ኢንርፔክተር ኢፋ(የስለላ ኃላፊ) እና ሌሎች የደህንነት አባላት
©voice of amhara