Breaking News
Home / Amharic / መከላከያ ተብዬው ተፈረካክሷል!

መከላከያ ተብዬው ተፈረካክሷል!

 
እመቤት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጨቅላው አቢይ አህመድ አማራን ትጥቁን ብቻ ሳይሆን ሱሪውን እናስፈታዋለን ብለው ያሰማሩት የኦሮሙማ ሰራዊት ተፈረካክሷል። ትጥቅ አስፈቺ ሳይሆን ትጥቅ ፈቺ ሁናል። ንፁሃንን ሊገድል ወደ አማራ ምድር የገባው ወታደር ከፊትም ከኋላም እሳት ሁኖበታል። ድንገት ሳያስበው በፋኖ መግቢያው እና መውጫው በቅፅበት ስለተዘጋበት ነፍስ ግቢ ነፍስ ዉጭ ላይ ነው፤ ለመሸሽ እንኳን እድል አላገኘም። አዲስ አበባን ከጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ የሚያገናኙ መንገዶች እና ከ30 በላይ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር ስለገቡ፣ ወደ አማራ ክልል የገባው የአቢይ ሰራዊት ትጥቅ፣ ስንቅ እና አጋዥ ሃይል ማግኘት አይችልም። እነ አቢይ አጋዥ ብለው በአውቶብስ እያሳፈሩ የሚልኩት ሰራዊትም ሰተት ብሎ ወጥመድ ውስጥ እየገባ፣ ትጥቁን እና ህይወቱን እየተቀማ ነው።
የባህር ዳር፣ ላሊበላ እና ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማሪፊያወች በፋኖ ቁጥጥር ስር ስለሆኑ ወይም በአቅራቢያቸው ውጊያ ስላለ በረራ አቁመዋል። የባህርዳሩ አዉሮፕላን ማሪፊያም በቀጣዮቹ ቀናት የመዘጋት እድሉ ሰፊ ነው፤ ፋኖ ከአውሮፕላን ማሪፊያው 30 ኪሜ ርቀት ያለችውን መራዊ ከተማ ይዟል። አዉሮፕላን ማረፊያውን መምታት ስላልተፈለገ እንጅ ፋኖ ከመከላከያ የቀማቸውን ከባድ መሳሪያወች ተጠቅሞ በረራ እንዲቆም ማድረግ ይችላል። ባህር ዳር ያለው መከላከያ በቀለበት ውስጥ ስለገባ አመራሮቹ አየር ማረፊያው ይዘጋል ብለው በመስጋት በአውሮፕላን ጥለውት ለመሸሽ ዝግጅት ላይ ናቸው። የተላላኪው ብአዴን ሰወችም መከላከያ ካምፕ ውስጥ አብረው ስለተከበቡ ሊሸሹ ተዘጋጅተዋል።
ባለፉት 3 ቀናት ብቻ በሽወች የሚቆጠር ወታደር ተገድሏል ወይም ተማርኳል። በየቦታው ተበታትኖ የተቆራረጠው ወደ 100 ሺ የሚሆን የኦሮሙማ ጨጫፊ ሰራዊት ያለው አማራጭ እጅ መስጠት፣ ካልሆነም በጦርነት ወይም በስንቅ እጦት መሞት ነው፤ መቸም ሊያጠፋው የዘመተበት የአማራ ህዝብ እንደ ትናንቱ ሰራዊቴ ብሎ ስንቅ አይሰጠውም።
አቢይ በቀቢፀ ተስፋ የአማራ ከተሞችን በጀት እና በድሮን ሊደበድብ ይችላል። ቢደብድብም ንፁሃንን እንደለመደው ይገድላል እንጅ የተቆረጠውን እና የተከበበውን ሰራዊቱን ማዳን፣ መሬት ላይ ያለውን ነገር መለወጥ አይችልም። አቢይ ያጣውን ሰራዊት ለመተካት በአዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ በደቡብ እና ሌሎች ክልሎች አዲስ ዙር የወታደር ምልመላ ሊጀምር ይችላል።
አማራንና አማራነትን ማሸነፍ ግን ዘበት ነው!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.