Breaking News
Home / Amharic / አማራን ስለማይወክል “ሕገ-መንግስቴ አይደለም” – ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

አማራን ስለማይወክል “ሕገ-መንግስቴ አይደለም” – ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራችንን ከገባችበት ቅርቃር ለማውጣት የምንከተላቸው አማራጮች ሕገ መንግሥታዊ አማራጮችን ብቻ ነው፣ ሌላው መንገድ አይታሰብም ብለዋል። በድጋሚ የአማራ ሕዝብና መላው ኢትዮጵያዊያን ያልተሳተፉበትን የትህነግ/ኦነግ የጫካ ሰነድ ልክ ቅቡልነት እንዳለው አገራዊ ሰነድ አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል።

ስለዚህ የአማራ ሕዝብ ለ25 ዓመት በትዕግስት ያቀረበው በህገ መንግስቱ ውስጥ ፍላጎቴ፣ መብቴና ጥቅሜ ይካተትልኝ የሚለው ህጋዊና ፍትሃዊ ጥያቄው በመንግስት በተደጋጋሚ ተቀባይነት ካላገኜና ውድቅ የሚደረግ ከሆነ፣ በዚህ ህገ መንግስት ላይ ተከታታይ የተቃውሞ ዘመቻ ከመጀመር ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖረንም ማለት ነው።

ስለዚህም:-

1) በመጀመሪያ ለቀጣይ አንድ ሳምንት የሚቆይ ተከታታይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መክፈት። የዘመቻው መሪ ቃልም “ሕገ-መንግስቴ አይደለም”/ “Not My Constitution”, #NotMyConstitution በሚል መሪ ቃል ወጥነትና ተከታታይነት ያለው ዘመቻና ተቃውሞ በፌስቡክ በአማርኛ፣ በትዊተር በእንግሊዘኛ ማካሄድ። በዩቲውብና በፌስቡክም የ30 ስከንድ ቪዲዩ በማዘጋጀት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አማራውን እንደማይወክለውና እንደማንቀበለው የሚገልጽ የአማርኛ/እንግሊዝኛና ሌሎች ቌንቋዎች መልዕክት ማስተላለፍ እንቀጥላለን።

2) በቀጣይ በምንስማማበት ቀን ጀምሮ ደግሞ መላው የአማራ ህዝብ በሚኖርበት አካባቢ ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል ፔቲሽን የማሰባስብና፣ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የማስገባት ስራ መስራት፣

3) በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የተካተቱትን ሂደቶች ሞክረን መንግስት ለአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ጆሮ የማይሰጥ ከሆነ፣ በቀጣይ የህገ መንግስቱን ቅጅዎች እያሰባሰቡ በአደባባይ የመቅደድ፣ የአማራ ተማሪዎች የክልልና ብሔራዊ መዝሙሮች ሲዘመሩ የመጮህና ተቃውሞ የማሰማት፣

4) እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ሰላማዊ የትግል ሂደቶች ተሞክረው በመንግስት በኩል እምቢተኝነቱ ከቀጠለ አማራው ሌሎችም ሰላማዊና በየደርጃው የሚደረጉ የተቃውሞ ርምጃዎችን ወደመቀጠል ይሽጋገራል።

አጀንዳ ሳንደራርብ ወደስራ!

*****
ሕገ መንግስቴ አይደለም!
#NotMyConstitution
ህገ መንግስት ይስተካከል፣ ይሻሻል ወይም ይቀየር!

አፓርታይዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክክለኛ ገጽታ!

(አቻምየለህ ታምሩ)

የአገሪቱ ከፍተኛው ባለሥልጣን ጠቅላይ ሚንስትሩ የተገኘበት ይህ መድረክ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው መድረኮች አንዱ ነው። በዚህ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሚወሰንባቸው መድረኮች አንዱ በሆነው «የለውጥ» ጉባኤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰባ ከመቶ በላይ የሚሆነውን ከሚሸፍኑት ሁለት ነገዶች አንዱ የሆነው አማራ ግን አልተወከለም ወይንም ባለጊዜዎቹ እንዲወከል አልፈለጉም ። ይህ በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም! ይህ አማራን ማግለል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትክክለኛ ገጽታ ነው። ላለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት የኖርነው ልክ በፎቶው ላይ እንደሚታየው በኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እንዳንሳተፍ ተቀሟዊ በሆነ መልኩ ተገለንና መንግሥታዊ እግድ ተጥሎብን ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአፓርታይድ ፖለቲካ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ ሊቀርብ አይችልም!

«ለውጡን እናግዝ» የሚሉን ሰዎች እናግዝ እያሉን ያለው ይህንን አማራ መቶ በመቶ ከጨዋታ ውጭ የተደረገበትን ሴራ ነው። ተጀመረ የሚሉን የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀፍ አግዙ እየተባልን ያለነው አማራን እንዲህ እያገለሉና እንዲገለል እያደረጉ ከአማራ የጸዳ አካባቢ ለመመስረት እንደተንቀሳቀሱ ሁሉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከአማራ ለማጽዳት እያደረጉት ያለውን የአፓርታይድ ተግባር ነው።

ከአማራው መካከል የወጡ የሌሎች ጉዳይ ፈጻሚዎችም በውጭም በውስጥም ሆነው ለአማራ አንዳች ነገር ጠብ ያለለት ይመስል «ለውጡን እናግዝ» በማለት ከአማራ አንጻር የቆሙ የአፓርታይድ አራማጆችን እያገለገሉ ያሉት አማራው ተጠናክሮ እንዳይደራጅ ማደንዘዝንና በላዩ ላይ የተጫነውም የአፓራይድ አገዛዝ አማራው መቶ በመቶ እ እንዲህ እያገለለ የሚያካሂደውን ፋሽዝም እንደለውጥ ቆጥረውት ነው።

እስቲ የተጀመረው የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀድ አግዙ ስትሉ የምትውሉ ለአማራው የትኛውን ነው ለውጡ? ከታች የምታዩዋቸው ስድስቱ ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከዛሬ ሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በሐምሌ 1983 ዓ.ም. በወያኔ፣ በሻዕብያና ኦነግ አጋፋሪነት አማራን አግልለው በኢትዮጵያ ምድር ሰላምንም ዲሞክራሲንም ለመቅበር በአፍሪካ አዳራሽ በተካሄደው «የሰላምና ዲሞክራሲ» ኮንፍረንስ በአንድም በሌላው መንገድ ተሳታፊዎች ነበሩ አልያም ወኪሎቻቸው ተሳትፈዋል። ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት ዋና ተዋናይ የነበረው ሻዕብያ በዚህ መድረክ ባይገኝም በኢትዮጵያ ጉዳይ ወሳኝ ሁኖ «ጠረጴዋው» ላይ ግን ዛሬም አለ። ዶክተር ብርሃኑም ቢሆን ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት የሽግግር መንግሥት ተብዮው ኮንፍረንስ ተሳታፊና ታዛቢ የነበረው የጉራጌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አባል ነበር።

ዛሬ የጎደለው መለስ ዜናዊ በአካል አለመኖሩና ከ27 ዓመታት በፊት በአምስት ድርጅቶች የተወከለው ኦሮሞ ዛሬ በሶስት ድርጅቶች መወከሉ ብቻ ነው። ሰዎቹ ኢትዮጵያን ቢወክሎ ጥያቄ ባልተነሳባቸው ነበር። ሆኖም ሰዎቹ የወከሉት ኢትዮጵያን ሳይሆን ነገዳቸውን ብቻ ነውና የተቀረው ነገድ በነሱ ውስጥ ራሱን ባያይ አይፈረድበትም።

ዛሬም፣ ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊትም ሁለት ተመሳሳይ ነገሮች ይታያሉ። አንዱ መለስ በአካል ባይኖርም የራዕዩን ተሸካሚዎች መድረኩ ከጫፍ እስከጫፍ መሙላታቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ ዛሬም ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊትም አማራው በመድረኩ አለመኖሩ ነው። ከሀያ ሰባት ዓመታት በፊት በአማራ ጥላቻ የናወዙት እነዚህ ስድስቱ ግለሰቦች ወይንም ወኪሎቻቸው አማራ እንዳይገኝ አድርገው ከፕሮግራማቸው በማውጣጣት ሕገ መንግሥት ያሉትን የቅሚያና የግድያ ደንብ አዘጋጅተው ነበር። እነሆ ዛሬ ከ27 ዓመታት በኋላ ስድስቱም የ27 ዓመታት የሥራ ውጤታቸውን ለመመረቅ በመድረክ ተገናኝተው ሽር ብትን እያሉ ናቸው።

እነዚህ ስድስቱ ዛሬ ከሀያ ሰባት ዓመታት በኋላ ለውጥ፣ ለውጥ እያሉ ቢሰብኩም የተለየ ውጤት እናመጣለብ ብለው እያታከቱን ያለው ግን አንዳች የመዋቅርና የሕግ ለውጥ ሳያካሂዱ በተመሳሳ መንገድ [በአብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ በጎሳ ፌድራሊዝም፣ ሕጋዊነት በሌለው ሕገ መንግሥት፣ ወዘተ] በመሄድ የመንፈስ አባታቸውን የመለስ ዜናዊን ራዕይ እያስቀጠሉ ነው። ዛሬም ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ እየተመሩ፣ አገዛዙ የተዋቀረበት ርዕዮተ ዓለም ሳይቀይቱና የመዋቅርና የአደረጃጀት ለውጥ ሳያደርጉ የተለየ ውጤት ሊያመጡና አገራዊ ተቋማትን ሊፈጥሩ ያስባሉ!

ደግነቱ ዛሬ ትናንት አይደለም! «ለውጡን እናግዝ» ብለው የተኮለኮሉት የኛዎቹ አደንዛኞችም ሆኑ ባለጉዳዮቻቸው እነ ዐቢይ ባይፈልጉትም የአፓርያድ አገዛዝ የወለደው አማራው ግን በሚገርም ፍጥነት ራሱን ለመታደግ በአንድ ላይ ተነስቷል፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሰማንያ ሶስቱ የፋሲካ ዶሮ ለመሆን ለዳግም እርድ የሚዘጋጅ አማራ የለም! የአገሩና የመንግሥት ባለቤት እስኪሆን ድረስ የጀመረውን የኅልውና ተጋድሎ ያለርሕራሔ ይቀጥላል!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.