ጋዜጠኛ ወግ ደረስ ጤናውና ዶክተር መዝገብ ጎጃም ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ህዝቡን አንቅተዋል። ከልክ በላይ የፋኖን እንቅስቃሴ አስጩሆታል፣ አገዛዙን በፕሮፖጋንዳ አፈር ከድሜ አብልቶታል፣ በምርኮኞች ላይም ሠፊ ግንዛቤ ሲፈጥር ከርሟል።
ይሁን እንጅ በርካቶችም ስማቸው የማይታወቅ ዘመነ ካሴ በሚመራው ጎጃም የአማራ ፋኖ ታፍነዋል። ኮረኔል ጌታሁንን ለማፈን ተብሎ ምን ያህል መስዋዕት እንደተከፈለ ማንም ያውቃል። ህግ ማስከበር እየተባለ የበርካታ ወንድሞቻችን ነፍስ በከንቱ እየተቀጠፈ ነው። ይሄ ነገር ደግሞ የተዳፈነ እሳት ሆኖ ነገ ላይ ይፈነዳና መበቃቀልን የዕለት ስራ ይሆንና ማህበረሰባዊ ቀውስ ያስከትላል።
ጎጃም ውስጥ አረ ወደየት አቤት እንበል ብለው ከእስር ቤት የመጣ ተብሎ የልጆች ምስል ደርሶኛል። ነገሩ ከነገ ዛሬ ይስተካከላል በሚል በዝምታ አልፈነው ነበር። አሁን ግን ነገሩ ሁሉ እየተለጠጠ ነው። ወንድም በወንድሙ ላይ መገዳደል የየዕለት ተግባር ሁኗል። በሀይል ልዩነትን ለማስተናገድ መሞከር ዳፋው ነገ ነው የሚሠማን። አሁን በጦርነት ላይ ስለሆንን ብዙም ላይገባን ይችላል። ከጦርነት በኃላ ግን ወገባችን ደቆ ነው የምናገኘው።
ስለሆነም በየትኛውም መንገድ ልዩነትን በሀይል ለማስተካከል መሞከር አደጋው ከባድ ነው። የሰላ ትችት ውይይት ሽምግልና መሳሪያዎቻችን ሊሆኑ ይገባል። የሚዲያው ማህበረሰብም ገና ለገና የመንጋ ዘመቻ ፈርቶ ዝም ከማለት እየተፈጠረ ያለውን አፍራሽ ፣ አጥፊ መንገድ ሊሞግት ይገባል። ዝም ማለት እንደማበረታት ይቆጠራል።
ድል ለህዝባችን‼