TimeLine Layout
August, 2019
-
20 August
19 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራሮችና አባላት በዋስትና ከእስር ተፈተዋል
የሰኔ 15ቱን ክስተት ተከትሎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአንድ ወር በላይ በእስር የቆዩ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮችና አባላት በዋስትና ከእስር ተፈቱ፣ **** የሰኔ 15ቱን ክስተት ተከትሎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከሰኔ 15ቱ የአማራ ሕዝብ መሪዎችና የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ግድያ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ከአንድ ወር በላይ በእስር የቆዩት 19 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራሮችና አባላት በዋስትና ከእስር ተፈተዋል።
Read More » -
20 August
አብን የእቴጌ ጣይቱንና የፊታውራሪ ገበየሁን የልደት በዓል በአብን ዋና ፅ/ቤት አከበሩ፤
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራሮች የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ፣ የእቴጌ ጣይቱንና የፊታውራሪ ገበየሁን የልደት በዓል በአብን ዋና ፅ/ቤት አከበሩ፤ ከነሃሴ 11-12/2011 ዓ.ም በተካሄደው የአብን ብሔራዊ ምክር ቤት ፩ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የታደሙ የምክር ቤቱ አባላትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ እና የፊታውራሪ ገበየሁን 175ኛ፣ የእቴጌ ጣይቱን ደግሞ 179ኛ የልደት በዓል ነሃሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም በአብን …
Read More » -
19 August
አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ ያለ) አክሲዮን ሽያጭ መግለጫ
አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት በአክሲዮን ሽያጭ ላይ ነው። በዚህም መሰረት ማንኛውም የባንኩ ባለቤት መሆን የሚፈልግ ግለሰብ እና ድርጅት ከዚህ በታች ስማቸው በተገለፁት ባንኮች በኩል አክሲዮኑን መግዛት ይችላል፡፡ አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል የአክሲዮን ግዢ ቅፅ በአማራ ባንክ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ወይም በዓባይ ባንክ አ.ማ. በሁሉም ቅ/መቤቶች ማግኘት ይቻላል፡፡ 1. የአንድ አክሲዮን መጠን ብር 1000 ( አንድ ሽህ …
Read More » -
19 August
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የብሔራዊ ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ማጠናቀቂያ የተሰጠ መግለጫ
** የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በአፈና አይገታም ! የህዝባችን ሁለንተናዊ ትግል አምጦ የወለደው አብን የአማራ ህዝብ መሰረታዊ የኅልዉና፣ የፍትኅና የእኩልነት ጥያቄዎችን በመለየትና አማራዉን በማደራጀት የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ በመቀልበስ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በእኩልነትና በፍትኃዊነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እየተንቅሳቀሰ ያለ ድርጅት ነዉ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ብሔራዊ ምክር ቤት ከነሃሴ 11-12/2011 ዓ.ም ሲያካሂድ የቆየውን የ1ኛ ዓመት …
Read More » -
18 August
የድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ሊያቀርበው ያሠበው ኮንሰርት ፍቃድ ተከለከለ።
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ መስቀል አደባባይ ላይ ሊያደርግ ያሰበው ኮንሰርት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍቃድ ሳያገኝ ቀረ። ኢትዮፒካሊንክ ከከተማው አስተዳደር ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት መስቀል አደባባይ ለፀጥታ ምቹ ባለመሆኑ ኮንሰርቱ ፍቃድ ሊሰጠው አለመቻሉን አስረድቷል። ነገር ግን የኮንሰርቱ አዘጋጆች በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርቱን ለማካሄድ ድጋሚ የፍቃድ ጥያቄ ማቅረባቸውን እና አስተዳደሩም ለዚህኛው ጥያቄ በሚቀጥለው ሳምንት ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን አስታውቋል። ቴዲ …
Read More » -
16 August
በማንነቴ ምክንያት ከስራ እና ከደሞዝ እንድታገድ ተደርጊያለሁ።
ጋዜጠኛ ደሳለው ጥላሁን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ውስጥ ከ 10 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በተለያዮ የስራ ኃላፊነት ደረጃዎች ላይ አገልግሏል፤ በቅርቡም ከሐምሌ 04 ቀን 2011 ዓ.ም ከሚሰሩበት ተቋም ከስራ እና ከደሞዝ ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንደታገደ ይገልፃል። ጉዳዮን በማስመልከት የአማራ ሚዲያ ማዕከል አቶ ደሳለው ጥላሁንን ስቱዲዮ ድረስ በመጋበዝ ቆይታ ያደረገ ሲሆን …
Read More »